‹‹ሁሉም የፀጥታ ኃይሎች የሕግ የበላይነት እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ››

SelamAbesha.com

በአክሱም የእደ ጥበብ ሙያተኞች ከቱሪዝም ዘርፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገለጹ

አክሱም ነሃሴ 21/2008 በአክሱም ከተማና አካባቢው የሚገኙ የመስህብ ስፍራዎችን ለሚጎበኙ ቱሪስቶች ስራዎቻቸውን እያቀረቡ በመሸጥ ተጠቃሚ መሆናቸውን አስተያየታቸውን የሰጡ የእደ ጥበብ ሙያተኞች ገለጹ፡፡

 

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የአካባቢው መስህብ ስፍራዎች ከጎበኙ የውጭና ሀገር ውስጥ ቱሪስቶች ከ143 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል፡፡

 

ወጣት ፊልሞን ተኪኤ በአክሱም ከተማ ልዩ ስሙ ሓወልት ተብሎ በሚጠራ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ከድንጋይ ፈልፍሎ የሀወልት ቅርጾች፣መስቀል ምሰልና ሌሎች የእደ ጥበባት ስራዎችን በመስራት እንደሚተዳደር ለኢዜአ ገልጿል፡፡ ፡

 

ስራዎቹንም ከተለያዩ ሃገራት ለሚመጡና ለሀገር ውስጥ ቱሪስቶች በሽያጭ በማቅረብ በወር በአማካኝ ሦስት ሺህ ብር ገቢ እንደሚያገኝ ተናግረዋል።

 

ወጣት ፊልሞን እንዳለው በሚያገኘው ገቢም የራሱንና የቤተሰቦቹን ኑሮ በአግባቡ እንዲመራ አስችሎታል፡፡

 

የተለያዩ የቤት ማስጌጫ የስፌድ እቃዎችን በማዘጋጀት ላይ የተሰማራችው ወጣት አልማዝ በየነ በበኩልዋ፣ከስራዎቿ ሽያጭ በወር አራት ሺህ ብር የሚጠጋ ገቢ እንደምታገኝ ተናግራለች፡፡

 

በዚህም ሁለት ልጆቿዋን ከማስተማር ባለፈ ከ60 ሺህ ብር በላይ መቆጠብ ችላለች፡፡

 

የጀመረችው ቁጠባ በማሳደግም ወደ ፊት ለጎብኝዎች የትራንሰፖርት አገልግሎት የሚሰጥ ሚኒባስ ለመግዛት እቅድ እንዳለትም ወጣት አልማዝ ገልጻለች፡፡

 

የፈረንሳይ ተወላጁ ዶክተር እስቲቨን ጆርጅ በሰጡት አስተያየት የአክሱም ታሪካዊ ስፍራዎችን ሲገበኙ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ጠቁመው ከተማዋ ለጎብኚዎች ምቹ መሆኗን ተናግረዋል።

 

"እግረኛ የሚሄድባቸው መንገዶችም በድንጋይ ንጣፍ ተውበው በመሰራታቸው ሳቢና ጽዱ ናቸው "ብለዋል።

 

ቀደም ሲል በልመና ተግባር ላይ በተሰማሩ ሰዎች፣በእደጥበብ ውጤት አቅራቢዎችና በአስጎብኝዎች ይፈጠሩ የነበሩ ወከባዎችም ዛሬ ላይ ስርዓት እንደያዙ መታዘባቸውንም ገልጸዋል፡፡

 

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በአክሱምና አከባቢው የሚገኙ ታሪካዊ ስራዎችን ከጎበኙ 66 ሺህ የውጭና የሀገረ ውስጥ ቱሪስቶች ከ143 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል፡፡

 

በአክሱም ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት የጎብኝዎችና መረጃ አስተባባሪ አቶ ተክለወይኒ ተስፋይ እንደገለጹት ከቱሪስቶቹ መካከል ከ19ሺህ 300 በላይ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች ናቸው፡፡

 

ገቢው ከ2007 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ12 በመቶ ብልጫ እንዳለውም አመልክተዋል።

 

አስተባባሪው እንዳሉት የመስህብ ስፍራዎችን ከማስተዋወቅ ባሻገር ቱሪስቶችን የሚያስተናግዱ ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው መሻሻሉ ጎብኚዎች እየተበራከቱ ለገቢው መጨመር አስተዋጽኦ ካዳረጉት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

 

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED