SelamAbesha.com

                

የፍቼ ጨምበላላ በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀዋሳ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ)

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2008 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲዳማ ብሔር ፍቼ ጨምበላላ የዘመን መለወጫ በዓልን በተለየ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው።


በዓሉ በአለም ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፊታችን ሰኔ 23 እና 24 በዋናነት በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡


ይህን ተከትሎም በሲዳማ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በዓሉ ለሁለት ሳምንት እንደሚከበር ተመልክቷል።


የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ለማ መለሰ እንደገለጹት፥ ቀደም ሲል በብሔሩ ተወላጆች ብቻ ይከበር የነበረው በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡



የፍቼ ጨምባላላ በሃገሪቱ በማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገበው የመስቀል በዓል ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) የተመዘገበው ባለፈው ህዳር ወር መሆኑ ይታወሳል።


Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED