የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መሥመር የኤሌክትሪክ ኃይል ሙከራ ተጀመረ

SelamAbesha.com

የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መሥመር የኤሌክትሪክ ኃይል ሙከራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ነሃሴ 17/2008 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የአዲስ አበባ-ሰበታ-ሚኤሶ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ፕሮጀክት የባቡር መሥመር የኤሌክትሪክ ኃይል ሙከራ መጀመሩን አስታወቀ።

 

የኮርፖሬሽኑ የኮሙኒኬሽንና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደረጀ ተፈራ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት ሙከራው እየተከናወነ ያለው የባቡሩን ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃቀምን ለመፈተሽ ነው።።

 

መሥመሩ የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር እንዳያጋጥመው ዝግጅት መደረጉንና ከሰበታ እስከ አዳማ ባለው መሥመር የኤሌክትሪክ አቅርቦት መሟላቱን ገልጸዋል።

 

ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ጋር ያላትን ትራንስፖርት አገልግሎት ለማሳለጥ በተዘረጋው መሥመር የሚንቀሳቀሱ 41 ሎኮሞቲቮችና 30 የመንገደኛ ባቡሮች ዝግጁ ሆነዋል።

 

ከአንድ ሺህ በላይ የጭነት ማጓጓዣዎች ድሬዳዋና ጅቡቲ ወደብ መድረሳቸውንም አቶ ደረጀ ተናግረዋል።

 

የባቡር መሥመሩ ከቻይና መንግስት በተገኘ የ3 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ብድር ነው የተገነባው።

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED