የቻይናው ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋን ቻኦ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው

SelamAbesha.com

የቻይናው ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋን ቻኦ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው

 

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2009 የቻይናው ምክትል ፕሬዚዳንት ሊ ዩዋን ቻኦ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትም በቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ዛሬ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሰላኝ ጋር ውይይት አድርግዋል።

የሁለትዮሽ ውይይቱን ተከትሎም በአዲስ አበባ የንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ለማስፋፋት የሚውል የብድር ስምምነትና የባቡር አካዳሚ ለመገንባት ከቻይና ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል ስምምነት ተፈርሟል።

ጉብኝቱ የህዝብ ለህዝብ ግንኙተቶችን ከማጠናከሩም ባለፈ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ስትራቴጂያዊ አጋርነት የሚያንጸባርቅ ነው ተብሏል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ በነገው እለትም በኢህአዴግ ምክር ቤት ጽ/ቤት በመገኘት ከኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር በፓርቲ ጉዳዮች ዙሪያ የሁለትዮሽ ውይይት እንደሚያካሂዱና ሲፒሲን በመወከል የፓርቲ ለፓርቲ ትብብር ስምምነት እንደሚፈራረሙ ተገልጿል።

ምክትል ፕሬዚዳንቱ የኢትጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባርና የቻይና ህዝብ ኮሙዩኒስት ፓርቲ በጋራ ያዘጋጁት ሴሚናር ላይ እንደሚሳተፉም ነው የተመለከተው።

የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር መስመርና የኢስተርን ኢንዳስትሪ ዞንን በመጎብኘት በኢትዮጵያ የሚኖራቸውን ቆይታ የሚጠናቅቁት ምክትል ፕሬዚዳንቱ ለጉብኝት ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ።

 

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED