SelamAbesha.com

ኦሕዴድ ሊቀመናብርቱን አነሳ

  የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሰሞኑን ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው፣ የድርጀቱን ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድርንና ምክትል ሊቀመንበሯን ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው ማክሰኞ መስከረም 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ እንዳሳወቀው፣ ሁለቱ አመራሮች ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል ከድርጅቱ ኃላፊነት እንዲነሱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡ በምትካቸውም የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ የሆኑን አቶ ለማ መገርሳን የኦሕዴድ ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ፣ በፌዴራል መንግሥት የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ደግሞ የኦሕዴድ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው ባወጣው መግለጫ ሁለቱ የድርጅቱ ሊቀመናብርት ከኃላፊነት የተነሱት ባቀረቡት ጥያቄ መሆኑን ቢገልጽም፣ የሪፖርተር ምንጮች ግን ሁለቱ ሊቀመናብርት በማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው በኦሮሚያ ተስፋፍተው ዓመቱን ሙሉ ለዘለቁ ግጭቶችና የኅብረተሰቡ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ያልቻሉ ናቸው በማለት  ሲወቅሳቸው እንደነበርና ሁለቱም አመራሮች ራሳቸውን መከላከል አለመቻላቸውን ገልጸዋል፡፡

አቶ ለማ መገርሳ ወጣት ከሚባሉት የኦሕዴድ አመራሮች ውስጥ አንዱ ሲሆኑ፣ ኦሕዴድን የተቀላቀሉት በ1983 ዓ.ም. እንደሆነና የትውልድ ቦታቸውም ወለጋ መሆኑን ምንጮች አክለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅትም የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ እንደሆኑም ይታወቃል፡፡

የኦሕዴድ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በወ/ሮ አስቴር ማሞ ምትክ የተሾሙት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ የፌዴራል ትራንስፖርት ሚኒስትር ሲሆኑ የትውልድ ቦታቸው ሻሸመኔ ነው፡፡

አቶ ሙክታርና ወ/ሮ አስቴር ከድርጅቱ ኃላፊነት ቢነሱም፣ አቶ ሙክታር የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ጨፌ ኦሮሚያ በጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ እስከሚሰበሰብ ይቀጥላሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በኦሕዴድ የቆየ የአሠራር ልማድ መሠረት የድርጀቱ ሊቀመንበር የክልሉ ፕሬዚዳንትነት ሥልጣን ያገኛል፡፡ በዚህ አሠራር የሚቀጥል ከሆነ ጨፌው በጥቅምት ወር መጀመርያ ላይ ሲሰበሰብ አቶ ለማ መገርሳን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ክላስተር አስተባባሪና የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስትርነታቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም በጥቅምት ወር መጀመርያ ሳምንት ላይ አዲስ ካቢኔ እስኪያዋቅሩ ድረስ ይቀጥላሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ መሆኑን የድርጅቱ መግለጫ ያመለክታል፡፡ በዚህ ስብሰባም ሹም ሽሮች እንደሚኖሩ እየተነገረ ነው፡፡ የደኢሕዴን ምክትል ሊቀመንበርና የትምህርት ሚኒትሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በበኩላቸው ከፌዴራል ተቋማት የተወጣጡ የኢሕአዴግ መካከለኛ አመራሮችን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በማወያያት ላይ ናቸው፡፡

  የሕወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ እየተካሄደ ነው

የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሰሞኑን ባካሄደው የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው፣ የድርጀቱን ሊቀመንበር አቶ ሙክታር ከድርንና ምክትል ሊቀመንበሯን ወ/ሮ አስቴር ማሞን ከኃላፊነት ማንሳቱን አስታወቀ፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው ማክሰኞ መስከረም 10 ቀን 2009 ዓ.ም. ምሽት ላይ በፌስቡክ ገጹ እንዳሳወቀው፣ ሁለቱ አመራሮች ያቀረቡትን ጥያቄ በመቀበል ከድርጅቱ ኃላፊነት እንዲነሱ በሙሉ ድምፅ ወስኗል፡፡ በምትካቸውም የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባዔ የሆኑን አቶ ለማ መገርሳን የኦሕዴድ ሊቀመንበር አድርጎ ሲመርጥ፣ በፌዴራል መንግሥት የትራንስፖርት ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁን ደግሞ የኦሕዴድ ምክትል ሊቀመንበር አድርጎ መርጧል፡፡

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED