SelamAbesha.com

                

ኮሚሽኑ የኤርትራ መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ አሳሰበ

ህዳር 2-2009

ኮሚሽኑ የኤርትራ መሪዎች ለፍርድ እንዲቀርቡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪ ኮሚሽን አሳሰበ፡፡


ኤርትራ ውስጥ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚመረምረው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሚደገፈው ኮሚሽን በዚያች ሃገር መሪዎች ተፈጽመዋል የሚባሉ ወንጀሎችን የሚመረምር ልዩ ችሎት እንዲመሰረት ጥሪ በማቅረብ ላይ ነው


ከመርማሪው ኮሚሽን ሦስት አባላት አንዷ የነበሩትና የመጀመሪያዋ የመንግሥታቱ ድርጅት የኤርትራ ጉዳይ ልዩ ራፖርተር ሺላ ኪታሩት ለቪኦኤ እንደገለጹት፤


ኮሚሽኑ በሪፖርቱ የሰዎች ደብዛ ማጥፋት ማሰቃየት፣ ያለፍርድ ሄደት ላልተወሰነ ጊዜ በእስር ማቆየት፣


እንዲሁም ርሸናን ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብዓዊ ተግባራት ስለመፈጸማቸው ማስረጃዎችን ዘርዝሮ አቅርበዋል።

ባለፈው ሰኔ ወር የወጣ አንድ የተባበሩት መንግሥታት ሪፖርት የኤርትራ መንግሥት መሪዎች ከሃያ በላይ ዓመታት በፊት “በሰብዓዊ ፍጡራን ላይ ወንጀል ፈጽመዋል” ማለቱ ይታወሳል (ቪ ኦ ኤ )፡፡


Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED