SelamAbesha.com

                

አዲሱ ዓመት በህዝብ በተለይም በወጣቱ የተነሱ ጥያቄዎችን መመለስ የሚችሉ ስር ነቀል ማሻሻያዎች የሚደረጉበት ጊዜ ይሆናል- መንግስት


አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 5፣ 2008 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲሱ ዓመት በህዝብ በተለይም በወጣቱ የተነሱ ጥያቄዎችን መመለስ የሚችሉ ስር ነቀል ማሻሻያዎች የሚደረጉበት ጊዜ ይሆናል አለ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት።


የኢፌዴሪ መንግስት ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች “እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሳችሁ ብሏል።


ጽህፈት ቤቱ አዲሱን አመት አስመልከቶ ባወጣው መግለጫው የተጀመረው የዕድገት ግስጋሴን የማቀዝቀዝ አቅም ያላቸው ስሜቶች የሚቀየሩበት እንደሚሆን ገልጿል።


ዲሞክራያዊ ስርዓት ግንባታችን የሚጎለብትበት፣ ኢኮኖሚያችንን ለማሸጋገር አቅም ያለው የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ትግበራ በሙሉ አቅም የሚፈፀምበት ጊዜም ይሆናል ነው ያለው።


የአገሪቱን የዕድገት ተስፋን ብሩህ ለሚያደርጉ እነኚህ የህዝብና የመንግስት ውሳኔዎች ተፈጻሚነት መላው ህዝብ  በአዲሱ በጀት ዓመት በአዲስ መንፈስ ከመንግስት ጎን መቆማቸውን እንዲቀጥሉ መንግስት ጥሪ አቅርቧል።

 


ሌሎች ዜናዎች:

« ኮሚሽኑ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ቃጠሎ ምክንያትና የእስረኞችን አያያዝ ሊያጣራ ነው   በዘመን መለወጫ አከባበር ላይ የእሳት አደጋ እንዳይከሰት ህብረተሰቡ ማብሰያዎችን በጥንቃቄ እንዲጠቀም ተጠየቀ »


Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED