ናይጄሪያ በቦኮሃራም መሪ አቡባከር ሸኩ ላይ ጥቃት አደረሰች

SelamAbesha.com

ናይጄሪያ በቦኮሃራም መሪ አቡባከር ሸኩ ላይ ጥቃት አደረሰች

ነሃሴ 17/2008 በአሸባሪ ቡድኑ ቦኮሃራም ላይ በተወሰደው የማጥቃት እርምጃ የቡድኑ መሪ አቡባከር ሸኩ መቁሰሉና ሌሎች የቡድኑ አመራሮችና አባላት መገደላቸውን የናይጄሪያ አየር ሃይል አስታወቀ፡፡

 

አየር ሃይሉ እንዳስታወቀው ሳምቢሳ በተባለው ደን አካባቢ በተወሰደ ጥቃት ነው መሪው ክፉኛ የቆሰለው፡፡

 

የአየር ሃይሉ ቃል አቀባይ ኮለኔል ሳኒ ካኩሸካ ኡስማን “ አቡባከር ሸኩ የተባለው የቡድኑ መሪ በደረሰበት ጥቃት ትክሻው አካባቢ ክፉኛ ተጎድቷል” ብለዋል፡፡

 

ጽንፈኛ ቡድኑ በናይጄሪያ ተደጋጋሚ የሽብር እንቅስቃሴዎችንና የጠለፋ ወንጀሎችን ሲያደርስ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

 

የናይጀሪያ መንግስትም ይህን ጽንፈኛ አሸባሪ ቡድንን ለማውደም ብርቱ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተነግሯል፡፡

 

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጆን ኬሪ ከፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ ጋር የሁለቱ ሃገራት ግንኙነት በሚጠናከርበትና በሃገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን ቦኮሀራም አሸባሪ ቡድንን ማውደም በሚቻልበት ዙሪያ ሊመክሩ ናይጄሪያ መግባታቸውም ታውቋል፡፡

 

ምንጭ፡ ሲሲቲቪ አፍሪካ

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED