ቦርዱ በሁከቱ የተጠረጠሩ 11ሺ 607 ሰዎች መታሰራቸውን አስታወቀ

SelamAbesha.com

ቦርዱ በሁከቱ የተጠረጠሩ 11ሺ 607 ሰዎች መታሰራቸውን አስታወቀ

ህዳር 2-2009

በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ  ከተደረገ አንስቶ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተፈጥሮ በነበረው ሁከት የተጠረጠሩ 11ሺ 607  ሰዎች  በስድስት ማዕከላት መታሠራቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጻም መርማሪ ቦርድ አስታወቀ ።

 

የመርማሪ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ታደሰ ሆርዶፋ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሠጡት መግለጫ እንደገለጹት፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በአገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሥራ ላይ እንዲውል ከተደረገ በኋላ 11ሺ 607 ሰዎች በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በተፈጠሩ ሁከቶች ላይ በመሳተፋቸው ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል ።

 

ከነዚሁም ውስጥ 11ሺ260ዎቹ ወንዶች ሲሆኑ ቀሪ 347ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል ፡፡

ቦርዱ ተጠርጣሪዎቹ በሙሉ ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ መሆናቸውን ጠቅሶ ፤ተጠርጣሪዎቹ ተማሪዎች አርሶ አደሮች ፣ነጋዴዎች እና ተቀጣሪ ሰራተኞች መሆናቸውን አስታውቋል ፡፡ 

 

ከዚህ ውጪ የታሰረ የውጭ ዜጋ እንደሌለ ሰብሳቢው በአጽንኦት ገልጸዋል ፡፡

ከፊንፊኔ ዙሪያ፣ ከሰሜን ሸዋና  ከምስራቅ ሸዋ  የተያዙት  1ሺ174 ታሳሪዎች በአዋሽ ማዕከል   ፣ ከቄሌም ወለጋ ፣ከአርሲ ፣ከምስራቅ ሸዋ ከምዕራብ አርሲ ዞኖች  የተያዙት 4ሺ 329  በጦላይ ማዕከል ፣ ከጉጂ ፣ ምዕራብ ሐረርጌ ፣ ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች የተያዙ  3ሺ 48  ታሳሪዎች በዝዋይ አላጌ ማዕከል ይገኛሉ ብለዋል ።

በተጨማሪም ከጌዲኦ አካባቢ የተያዙ 2ሺ114 ታሳሪዎች  በዲላና ይርጋለም ማዕከል ፣  ከሰሜን ጎንደር ከደቡብ ጎንደር ፣ ከምስራቅ ጉጃም እና ከሃዊ ዞኖች የተያዙት 532 ታሣሪዎች ደግሞ በባህርዳር ማዕከል የሚገኙ ሲሆን ፤ ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተያዙ 410 ታሣሪዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ማዕከል መታሰራቸውን አቶ ታደሰ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ።

 

ተጠርጣሪዎቹ እንዲታሰሩ የተደረጉበት በተለያዩ አካባቢዎች ሁከት በመፍጠር ፣ ሁከት በማነሳሳት ፣ ሽብር በመንዛትና አለመረጋጋት በመፍጠር፣ የግለሰቦችን ቤት  በማውደም ፣ ህዝባዊና መንግሥታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማቃጠልና ኢንቨስትመንትን  በማውደም ላይ  በመሠማራታቸው መሆኑን በመግለጫው ተጠቁሟል ።

 

በተጨማሪም የመንግስትን ፣የህዝብንና የግለሰቦችን ንብረትን በመዝረፍና በማቃጠል ማህበራዊ አገልግሎቶችን እንዲቋረጡ በማድረግ መሆኑን አስረድተዋል ፡፡

 

እንደሁም ቦንብና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን በጸጥታ ኃይሎች ላይ ጥቃት በማድረስ፣የጸጥታ ሃይሎችንና ግለሰቦችን በመግደል ፣ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በቅደድና በማቃጠል ፣የአሸባሪ ድርጅቶችን ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ እና የአሸባሪ ሃይሎችን የሽብር ቅስቀሳዎችን በማሰራጨት እና ህገ ወጥ የጦር መሳሪያን የመነገድና የማዛወር ድርጊትን በመፈጸም መያዛቸውን ገልጿል ፡፡

 

የታሳሪዎች የስም ዝርዝርና የሚገኙበት ማዕከል  በክልል መንግሥታት መዋቅር አማካኝነት ቤተሰቦቻቸው እንዲያውቁ  እንደሚደረግም  ቦርዱ  አመልክቷል፡፡

 

ከነገ  ጀምሮ የማሳወቅ ተግባሩም የሚፈጸም  መሆኑን  ሰብሳቢው አስታውቀዋል ።

የታሳሪ  ቤተሰቦች የተጠርጣሪዎች ስም ዝርዝሩ  ከተለጠፈበት ጊዜ ጀምሮ ወዳሉበት ማረፊያ ማዕከላት  በመሄድ   መጠየቅ የሚችሉ  መሆኑን  ገልጸዋል ።

 

የመርማሪ ቦርዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን  ተግባራዊ ለማድረግ ከተቋቋመው  የኮማንድ ፖስት  መረጃዎችን ያሳበሰበ መሆኑን ነው ያመለከተው ፡፡

በቀጣይም ይህን መረጃ  መሠረት በማድረግ የታሳሪዎችን የሰብዓዊ  መብት አያያዝ እንደሚገመግምና ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ቦርዱ ጨምሮ አስታውቋል ።

 

ቦርዱ የታሣሪዎችን ቁጥር፣ የተያዙበትን ቦታና በየትኛው ማዕከል እንደሚገኙ  ቅድሚያ ሠጥቶ  ለህዝብ ይፋ ያደረገው  የተጠርጣሪ ቤተሰቦችን የማወቅ  ህገ መንግሥታዊ መብት መሠረት  በማድረግ መሆኑን ነው ያስገነዘበው ።   

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች  ምክር ቤት ያቋቋመው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጻም  መርማሪ ቦርድ  ሰባት አባላት ያሉት መሆኑን ዋልታ ኢንፎርሜሽን ማዕከ

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED