በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ዙሪያ የሚመክር ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

SelamAbesha.com

በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ዙሪያ የሚመክር ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 7፣ 2009 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ትግበራ በአፍሪካ ስለሚኖረው አንድምታ የሚመክር ጉባዔ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው።

በ6ኛው የአፍሪካ ልማትና የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ይሆናል።

ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚሁ ጉባዔ የፓሪሱ ስምምነት በአፍሪካ ስለሚኖረው አንድምታ፣ ዕድሎችና ተግዳሮቶች ለመረዳት የመስኩ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ የተደረሰው ዓለም አቀፋዊ ሥምምነት የተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ከመጠናቀቁ አስቀድሞ ተግባራዊ እንደሚሆን ይጠበቃል።

ስምምነቱ የዓለምን የሙቀት መጠን ከኢንዱስትሪ አብዮት መምጣት በፊት ወደ ነበረው ደረጃ በ2 ዲግሪ ሴልሺዬስ ዝቅ ማድረግን ያከተተ ነው።

የፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት በለውጡ ተጠቂ ለሆነችው አፍሪካ የተለየ ትርጉም እንዳለውም ተገልጿል።

የአዲስ አበባው ጉባዔም ስምምነቱ ለአፍሪካ ምን ይዞ እንደሚመጣ የሚተነተንበት እንደሆነ ይጠበቃል።

ይህም የአፍሪካ አገራት በሞሮኮ ማራካሽ በመጪው ህዳር ከሚደረገው የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ አስቀድሞ ስትራቴጂክ ቅኝት መያዝ ያስችላቸዋል ነው የተባለው።በፓሪሱ የአየር ንብረት ለውጥ ስምምነት ዙሪያ የሚመክር ጉባዔ በአዲስ አበባ ይካሄዳል

 

Selamabesha.com

Hosted By Fissha Belay

© COPYRIGHT. ALL RIGHTS RESERVED